በካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጥሩ ፉክክር በታየበት የመጀመሪያ ጨዋታ አርሰናል ቼልሲን 3ለ2 አሸንፏል።
በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ቤን ዋይት ፣ ቪክቶር ዮኬሬሽ እና ማርቲን ዙብሜንዲ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል።
ለቼልሲ ተቀይሮ የገባው አሌሃንድሮ ጋርናቾ ሁለቱንም ግቦች በስሙ አስመዝግቧል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ከሦስት ሳምንታት በኋላ በኤምሬትስ ይከናወናል።
በሸዋንግዛው ግርማ