ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች ሁሌም አሸናፊ ሆና እንድትቀጥል ኅብረብሔራዊ አንድነቷን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች ሁሌም አሸናፊ ሆና እንድትቀጥል ኅብረብሔራዊ አንድነቷን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

AMN ጥር 07/ 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች ሁሌም አሸናፊ ሆና እንድትቀጥል ኅብረብሔራዊ አንድነቷን ማጠናከር እንደሚገባ የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአልን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ባካሄደው የማጠቃለያ ግምገማ ለበአሉ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና እና ምስጋና ሰጥቷል፡፡

መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው የዕውቅና ሰርተፍኬት የሰጡት የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች ሁሌም አሸናፊ ሆና እንድትቀጥል ለማስቻል ኅብረብሔራዊ አንድነቷን ማጠናከር እንደሚገባ ተልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በህብረት እውን ያደረጉት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጅክቶች በተከናወኑበት ማግስት የተከበረው የብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ልዩ የሚያደርጉት ነገሮች መኖራቸውን አፈ ጉባኤዉ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናግረዋል።

አፈጉባኤው አክለውም በተለይም የክልሎች እራስን የማስተዳደር መብት እውን በሆነባት የለውጡ ፍሬ የሆነችው የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአሉ መካሄዱን ጠቅሰው በዓሉ በተለይም ባለፉት ሰባት አመታት ሲከበር የቆየበት መንገድ እውነተኛ የፌደራል ስርአት ማሳያ ነው መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በድምቀት እንዲከበር የሀገሪቱን ገፅታ ለአለም በደመቀ መልኩ የማሳየቱን ስራ በመስራት አስተዋጽዖ ያበረከቱ አካላትን ያመሰገኑት አቶ አገኘሁ በተለይ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን በብዙ መልኩ ከፍተኛ አሻራቸውን ማኖራቸውን ጠቁመዋል።

በዕውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ስነሥርዐቱ ላይ የሁሉም ክልል አፈ ጉባኤዎች፣ የምክር ቤት አባላት እና የሚዲያ ከፍተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል በኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማእከላዊ ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት “ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ በሆሳእና ከተማ መከበሩ ይታወቃል፡፡

በቤተልሔም አየነዉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review