ኢትዮጵያ ከለውጡ ጋር በመጣ የቱሪዝም ንጋት እየደመቀች እና እየለማች ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ከለውጡ ጋር በመጣ የቱሪዝም ንጋት እየደመቀች እና እየለማች ነው  –  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN-ጥር 07/2018

የኢትየጵያ የዘመናት የቱሪዝም መዝገብ ሲገለጥ የሚነበበው በልኩ ያልደመቀ መልክዓ ተፈጥሮ፣ በወጉ ያልተገለጠ የታሪክ ግርማ፣ ሌማት ሆኖ ያልቀረበ ሃብት እና ውበት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ የመጣው ለውጥ ይህንን ሁሉ የዘመናት ችግር ከመሰረቱ የናደ አዲስ የቱሪዝም ልማት አምዶችን ያቆመ ነው ብለዋል፡፡

የለውጡ መንግስት ቱሪዝምን እንደ አንድ የኢኮኖሚ መሰረት በመውሰድ በትጋት ሰርቷል፡፡ አሁን የድካሙ ፍሬ እየተሰበሰበ፣ የሃገራዊ ጥረቱ አዝመራ እየታጨደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ለዚህም ድንቅ ውጤት የኢፌዲሪ ጠ/ሚ/ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዘርፉን በጠራ ራዕይ ተመልክተው፣ ለቱሪዝም የነበረውን እሳቤ ከማስተካከል ጀምሮ ሃገር እና ትውልድን ማዕከል ያደረገ አመራር በመስጠት የሰሩት ስራ የስኬቱ በር ከፋች ነው፡፡

ዛሬ በቱሪዝም ዘርፍ እያየን ያለነው ስኬት ሁሉ እንደ ቀን ንጋት የሚቆጠር የስኬት አሃዱ ነው ሲሉም በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው አጋርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review