የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ የሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ የፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ላይ እንደገለፁት፣ እንደ ገዥ ፓርቲ ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬታማ እንዲሆንና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል ።
ሁሉም የምርጫ ክልሎች ያለበት ደረጃ ተለይቶ ምርጫ ለማከናወን የሚያስችሉ የሰላምና ፀጥታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
እንደ ፓርቲ በምርጫው በብቃት ለመሳተፍ ዝግጅቶች መደረጉንም ተናግረዋል።
ባለፋት ስድስት ወራት የተከናወኑ የፓርቲ ስራዎች በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበትና ተሞክሮዎችም የተወሰዱበት መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል ።
የልማት ስራዎችን የህዝብን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መንገድ በመምራት ዘላቂ ሰላምንም ለማረጋገጥ የተደረጉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
የፓርቲው ሰው ተኮር ስራዎች አፈጻጸም የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ገልፀው በዚህም የህዝብ ተሳትፎ የላቀ እንደሆነ አብራርተዋል።

በየአካባቢው ያሉ እምቅ አቅሞችን ለይቶ በመጠቀም ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ትርክት እንዲጎለብት ተደርጓል በዚህም ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ተችሏል።
ባለፉት ስድስት ወራት የፓርቲ ዕሳቤዎችን በአግባቡ የተረዳ አመራር ለመፍጠር በተሰሩ ተግባራት የአመራር ብቃት አድጓል በዚህም የፓርቲ አደረጃጀትና አሰራር ማጠናከር ተችሏል ነው ያሉት ።
የወል ትርክት የበላይነት ለማስረፅ በሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን የተሰሩ ተግባራት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን አንስተዋል ።
አቶ አደም ፋራህ እንዳብራሩት ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የፓርቲውን የህዝብ ቅቡልነት ማሳደግ ተችሏል።

ፓርቲው የልማት ስራዎችን በብቃት መምራት በመቻሉ የህዝቡ አመኔታ ጨምሯል። ለዚህም ማሳያው በልማት ስራዎች በቀዳሚነት መሳተፉና ጥያቄዎቹንም በህዝባዊ መድረኮች በግልጽ ማቅረቡ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ መሆኑን ከብልፅግና ፓርቲ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል ።