በመዲናዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሃገር ዉስጥ ወደ ማምረት መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ

You are currently viewing በመዲናዋ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሃገር ዉስጥ ወደ ማምረት መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ

AMN ጥር 8/2018 ዓ.ም

ባለፋት ስድስት ወራት 238 ኢንዱስትሪዎች ከውጪ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሃገር ዉስጥ ወደ ማምረት እና መተካት መግባታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት አስታወቀ፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ በበጀት አመቱ አጋማሽ ልዩ ልዩ ድጋፎች መደረጋቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን የመሰረተ ልማት ፣ የመስሪያ ቦታና የፋይናንስ ማነቆዎችን ለመፍታት ባለፉት ስድስት ወራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ድጋፍ መደረጉን የቢሮው እቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር አቶ ያሲን ስምኦን ገልፀዋል።

በተሰራው ስራም 22 አምራች ኢንዱስትሪዎች የመስሪያ ቦታ ሲያገኙ 324 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ የመሰረተ ልማት ጥያቄያቸው ተፈቶላቸዋል። 1.4 ቢሊየን ብር የሚገመት የመስሪያ ሊዝ አቅርቦት ድጋፍ መደረጉንም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች ስትራቴጂክ የሆኑ ገቢ ምርቶችን ለመተካት በተሰራው ስራም 238 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርትን ወደ ማምረት ገብተዋል ነው ያለው ቢሮው።

19 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ምርቶቻቸውን ወደ ውጪ በመላክ ለሀገር የውጪ ምንዛሬ እያስገኙ እንደሚገኝ አቶ ያሲን ገልጸዋል። ባለፉት ስድስት ወራትም ከ16 ሺህ በላይ ቶን ምርት በመላክ 123 ሚሊየን ዶላር አስገኝተዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርትን በማምረት ፣ የውጪ ምንዛሬን በማስገኘትና የስራ እድል በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት እየጣሉ መሆኑም ነው በግምገማው የተመላከተው።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review