የፐብሊክ ፋይናንስ ማኔጅመንት ስትራቴጂው በሰው ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ አምጥቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸውም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ ለማድረግ ሲታሰብ ብዙዎች ዘንድ ፍራቻ እንደነበረ አንስተዋል።
ስትራተጂው በግልጽ እንዳስቀመጠው ኢትዮጵያ የምትፈጥራቸው ማንኛውም ሀብት ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ተገማችነት ባለው መንገድ ስራ ላይ ውሎ እያንዳንዱ ዜጋ በሚነገር የጥቅል ዕድገት ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው ብለዋል።
በሕገ-ወጥ መንገድ ይፈስ የነበረው እያንዳንዱ ሀብት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ለታለመለት ዓላማ በማዋል በሰው ሕይወት ላይ የሚታይ እና የሚጨበጥ ውጤት አምጥቷል ሲሉም ነው የተናገሩት።
የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ለዚህ ማሳያ እንደሆኑም ጠቁመዋል።
በቶለሳ መብራቴ