የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስታርፔይ/StarPay/ የተሰኘ አዲስ የክፍያ ሥርዓት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስታርፔይ/StarPay/ የተሰኘ አዲስ የክፍያ ሥርዓት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ
  • Post category:ዲጂታል

AMN-ጥር 08/2018 ዓ.ም

ስታርፔይ ፋይናንሺያል ሰርቪስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመሆን የዲጂታል ክፍያ ስረዓትን የሚያዘምን ስታርፔይ የተሰኘ ስረዓት ይፋ አድርጓል።

ስረዓቱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ ያገኘ መሆኑንም ስረዓቱ ይፋ በተደረገበት መድረክ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ተወካይና የኮርፖሬት አገልግሎቶች ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ አለም በፈጣን ቴክኖሎጂ እድገት እና እምነት ውስጥ እያለፈች እንደምትገኝ ጠቁመው በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት ጊዜን አና ጉልበትን ማባከን ታሪክ እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

በዘርፉ ይሰጡ የነበሩ አገልግሎቶች ወቅቱን በዋጀ የዲጂታል መተግበሪያዎች እየተተኩ እንደሚገኙ የጠቆሙት ኃላፊው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለዘርፉ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ እየሆነ መምጣቱንም ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገው የስታርፔይ ስርዓት ለደንበኞች የሚቀርቡ አገልግሎቶች የተገልጋዩን ፍላጎት ለማሟላት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

ስረዓቱ ለዚህ ይበቃ ዘንድ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን ያመሰገኑት አቶ ኤፍሬም ደንበኞቼ በመተግበሪያው ይጠቀሙበት ዘንድም ጥሪ አቅርበዋል።

የኤግላይንስ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በርሱፈቃድ ጌታቸው ስታርፔይ ነጋዴዎች በቀላሉ ክፍያዎቻቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለመሠብሠብ እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review