ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቤንች ሼካ ዞን አማን ከተማ ለሚኖሩ አካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አደረጉ

You are currently viewing ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቤንች ሼካ ዞን አማን ከተማ ለሚኖሩ አካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አደረጉ

AMN – ጥር 10/2018 ዓ.ም

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው እለት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሼካ ዞን አማን ከተማ ለሚኖሩ የአካል ጉዳተኞች የዊልቼር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የሚመራው የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ስራ ከጀመረበት ጌዜ ጀምሮ ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍም ልጆቻቸው የአካል ጉዳት ገጥሟቸው ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ ለተቸገሩ ወላጆችና ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለመማርም ሆነ ለመስራት ለተቸገሩ ወገኖቻች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review