የዓለም አቀፉ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል ፕሬዝዳንት የመቻል ስፖርት ክለብን ጎበኙ

You are currently viewing የዓለም አቀፉ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል ፕሬዝዳንት የመቻል ስፖርት ክለብን ጎበኙ

AMN ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም

የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ኒልቶን ጎሜዝ ሮሊም ፊልሆ ፣ የአፍሪካ ወታደራዊ ስፖርት ፕሬዝዳንት ሜጄር ጄኔራል መኪያኖ አብዱላሂ እና የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ዋና ፀሐፊ ሻምበል ሮቤርቶ ሬቺያ በጋራ በመሆን የመቻል ስፖርት ክለብን ግብኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ አንጋፋ እና ውጤታማ ከሆኑ ክለቦች መሀከል አንዱ የሆነው መቻል ስፖርት ክለብ በዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል አባል በመሆን ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዓለም እና በአፍሪካ ወታደራዊ ስፖርት ከፍተኛ አመራሮች ለጉብኝት መምጣታቸው በስፖርቱ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማሳየት እድል እንደሚፈጥር የመቻል ስፖርት ክለብ ስራ አስፈጻሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፉ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸዉ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል አባል መሆኗ ትልቅ እድል ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ወታደራዊ ስፖርት ካውንስል ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ኒልቶን ጎሜዝ በበኩላቸው የጉብኝቱ አላማ ስፖርቱን ማነቃቃት እና በቀጣይ እቅዶች ዙሪያ መወያየት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአለማየሁ ሙሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review