የቃና ዘገሊላ በዓል በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች በድምቀት ተከብሯል

You are currently viewing የቃና ዘገሊላ በዓል በአዲስ አበባ የተለያዩ አከባቢዎች በድምቀት ተከብሯል

AMN-ጥር 12/2018 ዓ.ም

በጥምቀት በዓል ማግስት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው “የቃና ዘገሊላ” በዓል በአዲስ አበባ በተለየያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል።

ይህ በዓል ከክርስቶስ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ሲሆን በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡

በዚህ ቃና በተባለ ቦታ ኢየሱስ ክርስቶ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም እና ከሐዋርያቱ ጋር ወደ ሠርግ ቤት ሄዶ፤ በሰርግ ቤቱ የነበረው የወይን ጠጅ በማለቁ ምክንያት ውሃውን ወደ ወይን በመቀየር የመጀመሪያ ተአምራቱን በማድረጉ የሚከበር በዓል ነው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review