የከተራ፣ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ኃይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀው በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብረዋል

You are currently viewing የከተራ፣ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ኃይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀው በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብረዋል

AMN ጥር 12/ 2018 ዓ/ም

የከተራ፣ የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓላት ኃይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀው በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብረዉ መጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ጠቅላይ መምሪያዉ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ በተከበረባቸው የከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ከከተራ ዕለት ጀምሮ በቴክኖሎጂ የታገዙ ተግባራትን አከናዉኗል።

የኃይማኖት አባቶች፣ የየአድባራቱ አስተዳዳሪዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ ልዩ ልዩ የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበራት እና የበዓሉ ታዳሚዎች እንዲሁም የከተማዋ የሠላም ሠራዊት አባላት ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመናበብ እና በቅንጅት ሰርተዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የበዓሉን ስኬትና ድምቀት በቅርበት ለመከታተልና ለህብረተሰቡ ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል በተለያዩ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ላይ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማቋቋም የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማዋቀርና ከፍትህ እንዲሁም ከጥምር የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ተግባር ወንጀልን እና የወንጀል ስጋቶችን መቆጣጠር ችሏል፡፡

መላው የከተማዋ ወጣቶች እና ምዕመኑ ከከተራው ዕለት ጀምሮ የቃና ዘገሊላ በዓል አከባበር እስኪጠናቀቅ ድረስ ከመንፈሳዊ አገልግሎታቸው ባሻገር ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ለበዓሉ ስኬታማነት በርካታ ተግባራትን በማከናወናቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አመስግኗል።

በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት ጠቅላይ መምሪያው ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review