አርሰናል ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ 7ኛ ተከታታይ ድል አስመዘገበ

You are currently viewing አርሰናል ኢንተር ሚላንን በማሸነፍ 7ኛ ተከታታይ ድል አስመዘገበ

AMN ጥር 12 ቀን 2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ 7ኛ ጨዋታ ኢንተር ሚላንን የገጠመው አርሰናል በጥሩ ብቃት 3ለ1 አሸንፏል።

በጁሴፔ ሜይዛ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን ሁለት ግቦች ጋብርኤል ጄሱስ አስቆጥሯል። ተቀይሮ የገባው ቪክቶር ዮኬሬሽ ሌላኛውን ግብ አስገኝቷል። ለኢንተር ሚላን ፔታር ሱቺች ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ሰባቱንም የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ያሸነፈው አርሰናል የሊግ ምዕራፍ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራ ጥሎ ማለፍ መቀላቀሉን አረጋግጧል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኪሊያን ምባፔ ሁለት ግቦችን ባስቆጠረበት ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ሞናኮን 6ለ1 ሲረታ የባለፈው የውድድር ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ፓሪሰን ዠርማ በስፖርቲንግ ሊዝበን 2ለ1 ተሸንፏል።

ቶተንሃም በክሪስቲያን ሮሜሮ እና ዶሚኒክ ሶላንኬ ግቦች ቦሩሲያ ዶርትመንድን 2ለ0 ሲያሸንፍ ፣ ኦሊምፒያኮስ ባየር ሊቨርኩሰንን በተመሳሳይ 2ለ0 መሸነፍ ችሏል።

ቪያሪያል አያክስን 2ለ1 ሲረታ ፣ ናፖሊ ከዴንማርኩ ኮፐንሃገን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 አጠናቋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review