የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ አመራሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ

You are currently viewing የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት እና የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ አመራሩ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ

AMN ጥር 13/2018

የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፤ የሚፈልገውን ዕድገትና ብልጽግናን ለማሳካት አመራሩ ገቢ አሰባሰብን ማሳድግ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ላይ በልዩ ትኩረት መስራት አለበት ብለዋል፡፡

አመራሩ በተመዘገቡ ድሎችና ስኬቶች ሳይመካ፣ ለላቀ ውጤት ራሱን ማዘጋጀትና ቀጣይነት ያለው ድል ለማስመዝገብ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል። በተለይም የቁጠባና የብድር ባህል እንዲዳብር አመራሩ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው፤ ያለ ገቢ እድገት ስለማይኖር፣ አመራሩ የገቢ አሰባሰብ ስራን በልዩ ትኩረት ሊያከናውን ይገባል ብለዋል፡፡

በተደጋጋሚ ተገምግመው መፍትሄ ያጡ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መንስኤ ተለይቶ ሊፈታ እና እንደሚገባ እና የሕዝብን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ የልማት ውጥኖችን (Initiatives) ማሳካት የግድ መሆኑን አጽኖት ሰጥተዋል።

የሚፈለገውን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሦስቱን የልማት አቅሞች ማለትም የግል፣ የመንግስት እና የሕዝብ አቅምን አቀናጅቶ ለጋራ ጥቅም ማዋል እንደሚገባ ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው ባለፉት ስድስት ወራት በሁሉም መስኮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውንና የመንግስት የማስፈጸም አቅምም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review