ደረጃውን ያልጠበቀ እና ለጤና ጎጂ የሆነ ጨው በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing ደረጃውን ያልጠበቀ እና ለጤና ጎጂ የሆነ ጨው በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN – ጥር 13/2018

ከ13 ሺህ ኩንታል በላይ ደረጃውን ያልጠበቀ እና ለጤና ጎጂ የሆነ ጨው በቁጥጥር ስር ዋለ።

አዮዳይዝድ ያልሆነና ንፅህናው ያልተጠበቀ የጨው ምርትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

ምርቱ የተቀመጠውን የአዮዲን መጠን ባለመያዙና ባለመታጠቡ ለሰው ልጅ ጤና ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ነው።

ባለስልጣኑ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ከ13 ሺህ በላይ ኩንታል የጨው ምርትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ምርቱ ፉሪ በሚገኙ ሁለት መጋዘኖች የተገኘ ሲሆን፣ ሶስት አምራቾች የተሳተፉበት እንደሆነም ተገልጿል። ባለስልጣኑ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ላብራቶሪዎችን አቋቁሞ የጥራትና ደህንነት ቁጥጥር ስራን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጾ፤ አምራቾች ህጋዊ አሰራርን በመከተል ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

ለህብረተሰብ ጤና ጠንቅ የሆኑ መሰል ተግባራትን ለመቆጣጠር የህብረተሰቡ ትብብር ወሳኝ በመሆኑ፣ ማንኛውም ሰው ጥቆማውን በአፋጣኝ ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ አፅንኦት ተሰጥቷል።

ጥቆማዎችን በ8482 ነፃ የስልክ መስመር ማድረስ እንደሚቻልም ተገልጿል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review