ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከሆኑት ሩስላን ናሲቦቭ እና የUN-HABITAT የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ከሆኑት ኦውማር ሲላ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከሆኑት ሩስላን ናሲቦቭ እና የUN-HABITAT የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ከሆኑት ኦውማር ሲላ ጋር ተወያዩ

AMN- ጥር 13/2018 ዓ. ም

በአዘርባጃን ባኩ ከተማ በሚካሄደው የዓለም ከተሞች ፎረም ላይ ከተማችን አዲስ አበባ ያላትን ተሞክሮ የምታካፍልበትን ሁኔታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ከሆኑት ሩስላን ናሲቦቭ እና የUN-HABITAT የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ከሆኑት ኦውማር ሲላ ጋር ዛሬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ መድረኩ መዲናችን አዲስ አበባ በዘርፉ ልምዷን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የምታካፍልበት እና ተሳትፎዋን ይበልጡን የምታሳድግበት ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል ብለዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጣይ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ዝግጅት፣ ከባኩ ልምድ የምንቀስምባቸውን መንገዶች በተመለከተ ፍሬያማ ዉይይት አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።

አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሁም የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል::

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review