ደቡብ ኮሪያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ህግ በማውጣት በዓለም ቀዳሚ ሀገር ሆነች

You are currently viewing ደቡብ ኮሪያ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ህግ በማውጣት በዓለም ቀዳሚ ሀገር ሆነች

AMN- ጥር 14/2018 ዓ.ም

ደቡብ ኮሪያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በዝርዝር የሚቆጣጠር አጠቃላይ ህግ ስራ ላይ በማዋል በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗ ተገልጿል፡፡

የሀገሪቱ የሳይንስ ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው “AI Basic Act” የተሰኘው ይህ ህግ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ስራ ላይ እንደሚውል ዩፒ አይ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል፡፡

የአይ ኤል ኩባንያዎች በቴክኖሎጂያቸው ለሚፈጠሩ የሀሰተኛ ምስሎች (Deepfakes) እና የተሳሳቱ መረጃዎች ከፍተኛ ተጠያቂነት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

ህጉ ማንኛውም በኤ አይ የተሰራ ምስል፣ ድምጽ ወይም ቪዲዮ መሆኑን የሚገልጽ ግልጽ ምልክት እንዲኖረው እንደሚያስገድድም ተገልጿል፡፡

እንደ OpenAI (ChatGPT) እና Google ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች በደቡብ ኮሪያ ውስጥ ህጋዊ ተወካይ እንዲኖራቸውም በህጉ ተካተኳቷል፡፡

ህጉን በሚጥሱ ተቋማት ላይ መንግስት ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት የመጣልና የማጣራት ስልጣን ተሰጥቶታል ተብሏል።

ይህ እርምጃ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ሳያደናቅፍ፣ የሰዎችን ደህንነትና መብት ለማስጠበቅ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ እንደሆነ መገለጹን ዩፒ አይ በመረጃው አስነብቧል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review