AMN ጥር 15/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ወደፊት መብረር፣ የጋራ ነገን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የአቪዬሽን ኤክስፖዉ በማደግ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በተሰናዳው የአቪዬሽን ኤክስፖ 2026 መክፈቻ ላይ ተገኝቻለሁ ብለዋል፡፡
“ወደፊት መብረር፣ የጋራ ነገን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ኤክስፖ የአቪዬሽን ቴክኖሎጂን፣ ክህሎትን፣ ትብብርን የማሳደግና በማደግ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ የአፍሪካ አቪዬሽን ማዕከልነት ሚናን ለማጠናከር የሐገር ውስጥ እና የውጭ ተባባሪ አካላትን በአንድ መድረክ ያገናኘ ነው ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡