ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካዊያን የነፃነትና የድል ጮራን የፈነጠቀች ታላቅ ሀገር መሆኗን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካዊያን የነፃነትና የድል ጮራን የፈነጠቀች ታላቅ ሀገር መሆኗን የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ

AMN ጥር 15/ 2018 ዓ.ም

“የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 90ኛውን የአየር ኃይል ቀንን በማስመልከት የጋራ ሥራዎቻችንን አጠናክረን የተረጋጋ አለምን እንገባ በሚል መሪ ሀሳብ ሶስተኛው 2026 የአፍሪካ አየር ኃይል ፎረም በቢሾፍቱ ከተማ ሆራርሰዴ አዳራሽ ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአይበገሬነት፣ በድል አድራጊነትና የጠላትን የማድረግ አቅም በማደባየት በዘመናት መካከል ኢትዮጵያን በማፅናት የታላቅ ሀገር ታላቅ ተቋም መሆን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተለይም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት ለአየር ኃይል በሰጠው ልዩ ትኩረት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰው ኃይል ግንባታ ፣ በውጊያ መሠረት ልማትና ሌሎች በርካታ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላለፉት 8 አመታት የኢትዮጵያን ታላቅነት የሚመጥን አየር ኃይል ለመገንባት ሥራዎችን መስራት በመቻሉ ተቋሙ አመርቂ ስኬት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ዋና አዛዡ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት በመሆን ለአፍሪካዊያን የጋራ ዕድገት እና አንድነት በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በፎረሙ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የአየር ኃይል አዛዦች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ የወታደራዊ አቭዬሽን ትጥቅ አምራች ኩባንያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታዉን የሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review