በመዲናዋ አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጅ በመደገፍ እና ብልሹ አሠራርን በመቅረፍ የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ ተችሏል

You are currently viewing በመዲናዋ አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጅ በመደገፍ እና ብልሹ አሠራርን በመቅረፍ የተገልጋይ እርካታ ማሳደግ ተችሏል

AMN – ጥር 16/2018 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸምን እየገመገመ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉ የሥራ ኃላፊዎች እንደገለጹትም ባለፉት ስድስት ወራት አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመን እና የተገልጋይ እርካታን ከማሳደግ አንፃር ተጨባጭ ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ እንደገለጹት በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ጣራ ስር በማድረግ አገልግሎትን በመስጠት የነዋሪዎችን እንግልት መቀነስ ተችሏል፡፡

የመሶብ አገልግሎትን ለማስፋት ቴክኖሎጅን ከሙያዊ ሥነ ምግባር ጋር ያሰናሰሉ ሠራተኞችን በማብዛት፣ እንዲሁም ብልሹ አሠራርን በመቅረፍ፣ በሌላ መልኩ ደግሞ በመንግስት እና በሕዝብ መካከል መተማመንን መገንባት በቀጣይም በትኩረት ይሠራል ብለዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ደግሞ በክፍለ ከተማዉ ባለፉት ስድስት ወራት ሁለንተናዊ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

ልማት፣ አገልግሎት አሰጣጥ እና መሰል ዘርፎች አመርቂ ዉጤት እንደተገኙባቸውም ገልጸዋል፡፡

የመንግስትን አቅም ከኅብረተሰቡ ጋር በማጋመድ ባለፉት ወራት በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ በጎ ፈቃድ እና የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ ናቸዉ፡፡

ስኬቶችን በቀጣይ ወራትም ለማስመዝገብ ሁለንተናዊ ርብርብ እንደሚደረግ የሥራ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review