ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ እና መሰረተ ልማቶችን እዉን ከማድረግ አኳያ ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል

You are currently viewing ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ እና መሰረተ ልማቶችን እዉን ከማድረግ አኳያ ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል

AMN – ጥር 17/2018 ዓ/ም

ባለፉት ስድስት ወራት በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን ከማጠናቀቅ እና መሰረተ ልማቶችን እዉን ከማድረግ አኳያ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ገለፁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃጸምና የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ የግምገማ መድረክ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉ የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የመዲናዋን ዕድገት የሚያስቀጥሉ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሀብተ ማሪያም ባለፉት ስድስት ወራት የጤና መሰረተ ልማቶችን በመገንባት የጥበብ ማዕከላትን ወደ ስራ በማስገባት የትምህርት ተቋማትን በመስራት እንዲሁም በሁሉን አቀፍ የመሰረተ ልማት እና የፕሮጀክቶች ግንባታ ተጨባጭ ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

ለስኬታማ ጉዞዉ የአመራሩ ቅንጅታዊ ስራ ትልቅ ስፍራን ይወስዳል ያሉት ኢንጂነር አያልነሽ፤ በቀጣይም ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ባለፉት ስድስት ወራት የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችል ተጨባጭ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል።

የመዲናዋን ነዋሪዎች የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለማጣጣም በበጀት አመቱ ከመቶ ሺ በላይ ቤቶች በመንግስት የግል አጋርነት፣ በማኅበር ፤በሪል ስቴትና በግል የቤት ልማት አማራጭ በትኩረት እየተሰራ ይገኛሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙህዲን ረሻድ፤ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የመዲናዋን የትራንስፖርት ሥርዓት የሚያሳልጥ የመንገድ መሰረተ ልማት መገንባቱን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዘሪሁን አባተ በበኩላቸዉ የመዲናዋን ለንፁሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፍላጎት ምላሽ መስጠት የሚያስችል መሠረት መጣሉን ገልጸዋል።

በቀጣይም ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በመቅረፍ ለሁለንተናዊ ስኬት እንደሚሰራ የተቋማት ሀላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review