በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለውበት ብቻ ሳይሆን ለከተማ ግብርናም አዲስ ተስፋ ሆኗል

You are currently viewing በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለውበት ብቻ ሳይሆን ለከተማ ግብርናም አዲስ ተስፋ ሆኗል

AMN- ጥር 18/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ለከተማዋ ውበት ብቻ ሳይሆን ለከተማ ግብርና መነቃቃት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ መሠረት እየጣለ መሆኑ ተገለጸ።

ባለፉት ሰባት ዓመታትም ከ1.1 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የከተማዋ አርሶ አደር እና የከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስታውቋል።”

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤፍኤም 96.3) ራዲዮ እንደገለጹት፣ በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉት የወንዝ ዳር ልማት ሥራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርና የኮሪደር ልማቱ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እያስገኙ ይገኛሉ።

ተበላሽተው የነበሩትን የመዲናዋን ወንዞች ያጸዳው የወንዝ ዳርቻ ልማት፤ ለአሳ እርባታ እና ለአትክልት መስኖ ልማት ዘርፎች ከፍተኛ ጥቅም እያስገኘ ነው።

በኮሪደር ልማቱ የሚተከሉት አበቦችና በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ የሚተከሉ የሚበሉ ተክሎች ለንብ እርባታ ሥራ ውጤታማነት የጎላ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አቶ መሐመድ አመልክተዋል።

የከተማ ግብርና ዘርፉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የገለጹት አቶ መሐመድ፣ ዘርፉ ከቤተሰብ የምግብ ፍጆታነት ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩንም ተናግረዋል።

ከ7 ዓመት በፊት ከ110 ሺህ ላልበለጡ ዜጎች ብቻ የሥራ ዕድል የፈጠረው የከተማ ግብርና፣ ባለፉት 7 ዓመታት ብቻ ከ1.1 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል።

በሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review