AMN- ጥር 18/2018 ዓ.ም
የጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን አደገኛ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን በይፋ አስታወቀ።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠር በዓለም ጤና ድርጅት የተቀመጠው አስገዳጅ የ42 ቀናት ከበሽታ ነጻ የመሆን ጊዜ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስመለክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ለሕከምና በመጡ ታማሚዎቸች ላይ በተደረገ ምርመራ፣ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን ያሳወቀው ሚኒርቴሩ፣ አሁን ላይ የመከላከል ስራው በስኬት እንደተጠናቀቀ አስታውቋል።
በዚህም፣ ቫይረሱ ከተከሰተበት እለት ጀምሮ 3 ሺህ 800 ሰዎች ላይ የላብራቶሪ ምርመራ አድርጎ 14ቱ በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጫለሁ ያለ ሲሆን፣ በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ 9 ሰዎች ሲሞቱ 5 የሚሆኑት ማገማቸውን አስታውቋል።
በማብሰሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የየክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ተገኝተዋል።
በጺዮን ማሞ እና ቶማስ አሊጋዝ