AMN ጥር 18/2018 ዓ.ም
በቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ የተመራ የልዑካን ቡድን በBRICKS ሃገራት መካከል WILL FOR PEACE 2026 በሚል በደቡብ አፍሪካ ሲካሄድ በነበረው የባህር ላይ ልምምድ ተካፍሏል፡፡
በቻይና መሪነት በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በነበረው የባህር ላይ ልምምድ በመሳተፍ በቀጣይ ከBRICKS ሀገራት ጋር ያለዉን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚጠቅሙ ግብዓቶችን ወደ ሀገሪቱ በማምጣት ተሳትፎውን አጠናቆ ተመልሷል፡፡

ከልምምዱ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አዛዥ ከደቡብ አፍሪካ ባህር ኃይል አዛዥና ከራሽያ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱም የኢትዮጵያ ባህር ኃይልን በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ለመደገፍ የሁለትዮሽ ስምምነት አድርገዋል፡፡
በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተሳተፉ የሁሉም የBRICKS ሀገራት አዛዦች በልምምዱ የተሳተፉ ባህርተኞችን ጎብኝተዋል።
የባህር ላይ ልምምዱን አስመልክተው የየሀገራቸውን የባህር ላይ ተጠቃሚነትና የወደፊት ፍላጎት ያመላከተ መልዕክት ማስተላለፋቸዉን የሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያሳያል።