ሰማንያ የሽብር ቡድኑ አመራርና አባላት እጅ ሰጡ

You are currently viewing ሰማንያ የሽብር ቡድኑ አመራርና አባላት እጅ ሰጡ
  • Post category:ወቅታዊ

AMN ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም

በምስራቅ ጉጂና ምስራቅ ቦረና ዞኖች 80 የኦነግ ሸኔ አመራርና አባላት እጅ መሥጠታቸውን የደቡብ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ግርማ አየለ ተናግረዋል።

የቡድኑ መካከለኛ አመራርና አባላት ጫካ ለጫካ እየተሹለከለኩ በሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚያደርሱት ያልተገባ ድርጊት አግባብ አለመሆኑን በመረዳት ሠላማዊ ህይወትን በመምረጥ እጅ እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

ሠራዊቱ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በተቀናጀ መንገድ የቀጠናውን ሠላም በማረጋገጥ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የኮሩ ሠራዊት የሚያጋጥሙትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን በጥበብ ተሻግሮ ለድል የሚያበቃው ሞራላዊና ስነ ልቦናዊ ዝግጁነትን እንደተላበሰ አዛዡ ተናግረዋል።

የምስራቅ ጉጂ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቦጌ ታፈሰ በበኩላቸው የክልሉ ፀጥታ ሃይል ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር ለቀጠናው ሠላምና መረጋጋጥ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ መግለጻቸዉን የሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review