የምርት ግብይት ሰንሰለቱን ጤናማ በማድረግ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ እንዲገናኙ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የምርት ግብይት ሰንሰለቱን ጤናማ በማድረግ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ እንዲገናኙ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥር 19/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽ ያስገነባው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ማቀዝቀዣ መጋዘን እና የገበያ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎንፌ (ዶ/ር) እና ሌሎች ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል፡፡

በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የምርት ግብይት ሰንሰለቱ ጤናማ እና አጭር በማድረግ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ እንዲገናኙ የማድረግ ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት ጤናማ እና ንጹህ የግብርና ምርቶች ለዜጎች እንዲቀርቡ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች ዛሬ ለምርቃት የበቃው የአትክልትና ፍራፍሬ መጋዘን ለሸማቹ ንጽህናቸውን የጠበቁ ምርቶችን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ማዕከሉ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማን ነዋሪ ቀዳሚ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ያብራሩት ከንቲባዋ

ከማዕከሉ የሚወጡ ምርቶች ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ አነስተኛ ሱቆችን በማደራጀት ከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

በከተማዋ አምስቱ በሮች የተገነቡ የገበያ ማዕከላት ለሸማቹና ለአምራቾች ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውን ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች ይህም በቂ ባለመሆኑ የግብርና ምርቶች ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የዓለም ገበያንም ተደራሽ እንዲያደርጉ ጥራት ላይ መስራት ይባል ብለዋል፡፡

በትስስር እና በጋራ በመስራ ብሎም ኃላፊነቶችን በአግባቡ በመወጣት ምርቶችን ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባም ከንቲባ አዳነች ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በውስጡ ዘመናዊ የማቀዝቀዣ መጋዘን እና ሁለገብ የህንጻ ፕሮጀክትን መያዙን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በሀይሉ ንጉሴ ናቸው፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም ፕሮጀክቱ 1.7 ቢሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት ጠቁመዋ፡፡

የምርት ማቀዝቀዣ መጋዘኑ በአንድ ጊዜ ከ20ሺ ኩንታል በላይ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን በዘመናዊ መንድ በማቀዝቀዝ እና በማቆየት የምርት ጥራት ደረጃን በመጠበቅ፣ የምርት ብልሽት እና ብክነትን በመቀነስ ምርቶች ጥራታቸውን እንደጠበቁ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ብሎም ለአምራቹ አስተማመኝ ገበያን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀዝቀዣ መጋዝኑ እና ሁለገብ የህንጻ ፕሮጀክቱ በ11 ሺህ 437 ካሬ መሬት ላይ ያረፈ መሆኑም ተመላቷል፡፡

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review