የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋታዎች

You are currently viewing የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመጨረሻ ጨዋታዎች

AMN ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ።

ቤኔፊካ ከሪያል ማድሪድ ፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከ ኢንተር ሚላን ፣ ናፖሊ ከቼልሲ እንዲሁም ፓሪሰን ዠርማ ከ ኒውካስትል ዩናይትድ የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች የበለጠ ትኩረት ስበዋል።

ናፖሊ በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም ቼልሲን በሚያስተናግድበት ጨዋታ አንቶኒዮ ኮንቴ የቀድሞ ክለባቸውን ይገጥማሉ።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ በቼልሲ ቆይታቸው የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ እንደነበሩ ይታወሳል።

በስምንት ነጥብ 25ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ናፖሊ በውድድሩ ለመቆየት የግድ ማሸነፍ ይጠበቅበታል። በ13 ነጥብ 8ኛ ደረጃ የተቀመጠው ቼልሲ በአንፃሩ በቀጥታ ሃላፊ ለመሆን ሦስት ነጥቡ ያስፈልገዋል።

ፓሪሰን ዠርማ ከኒውካስትል የሚያደርጉት ጨዋታ ለሁለቱም ክለቦች አስፈላጊ ነው። ቡድኖቹ ከመጀመሪያው ስምንት ደረጃ ላለመውጣት ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

በውድድሩ እስካሁን በተከናወኑት የ7ዙር ጨዋታዎች አርሰናል እና ባየርን ሙኒክ በቀጥታ ጥሎ ማለፍ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።

በውድድሩ ፎርማት መሰረት ስምንት ቡድኖች በቀጥታ ጥሎማለፍ ይገባሉ። ከ9-24 የሚጨርሱ ደግሞ እጣ ወጥቶላቸው እርስ በእርስ በመጫወት አሸናፊ ስምንት ቡድኖች ያልፋሉ።

ከ25-36ኛ ደረጃ የሚጨርሱት ደግሞ ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ።

የቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ደረጃን ሁሉንም ጨዋታ ያሸነፈው አርሰናል በ21 ነጥብ ሲመራ ባየርን ሙኒክ በ18 ነጥብ ይከተላል። ሪያል ማድሪድ ፣ ሊቨርፑል ፣ ቶተንሃም ፣ ፓሪሰን ዠርማ ፣ ኒውካስትል እና ቼልሲ በቀደም ተከተል እስከ ስምንት ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ደግሞ የሪያል ማድሪዱ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ 11 ግቦቹን በማስቆጠር ይመራል።

ዛሬ የሚከናወኑት 18ቱም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይጀምራሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review