“ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ እንዳላት ተመልክቻለሁ’’ ባካሪ ሳኛ

You are currently viewing “ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ እንዳላት ተመልክቻለሁ’’ ባካሪ ሳኛ

AMN ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትጥቅ አቅራቢ ማክሮን ጋር ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ባካሪ ሳኛ ሀገሪቱን የማወቅ እድል በማግኘቱ ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡ የቀድሞ የአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ኢትዮጵያን ከሩቅ እንጂ መጥቶ የማየት አጋጣሚ እንዳልነበረው ገልጿል፡፡

“እዚህ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝ ፤ ከሩቅ ሆኜ እናደማውቀው አይደለም ፤ በአካል ተገኝቼ ያየሁት ነገር ያለውን ትርክት የሚቀይር ነው፡፡ ሕዝቡ ትልቅ ክብር ያለው እና በጋራ የሚሰራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ” ሲል ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትጥቅ አቅራቢ ማክሮን መለያውን በሸራተን አዲስ ሲያስተዋውቅ የታደመው ባካሪ ሳኛ በተለይ የሕዝቡ አቀባበል እንዳስደመመው ጠቅሷል፡፡

“እውነት ለመናገር ቤቴ እንዳለሁ እንዲሰማኝ ነው ያደረጋችሁት ፤ ሀገራቹህ ትልቅ ተስፋ አላት ብዙ ነገር ከጠበቅኩት በላይ ሆኖብኛል፡፡” በማለት ሃሳቡን አካፍሏል፡፡

ከእግርኳሱ ጋር በተገናኘም ትክክለኛው ሰው በትክክለኛ ቦታው ላይ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባል ብሏል፡፡ “ጥሩ ጅምሮች አይቻለሁ ፤ እኔም በቻልኩት መጠን ለመርዳት ዝግጁ ነኝ፡፡ ስኬታማ መሆን የሚያስችል ግብዓቶች አላቹህ ፤ ውጤት ለማምጣት ግን ትዕግስት ያስፈልጋል፡፡” ሲል ሞያዊ ሃሳቡን አጋርቷል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review