በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እነማን አለፉ?

You are currently viewing በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እነማን አለፉ?

AMN ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ወደ ጥሎ ማለፍ በቀጥታ ካለፉ ስምንት ክለቦች አምስቱ ከእንግሊዝ ሆነዋል።

ስምንቱንም ጨዋታዎች አሸንፎ ታሪክ የሰራው አርሰናል ፣ ሊቨርፑል ፣ ቶተንሃም ፣ ቼልሲ እና ማንችስተር ሲቲ በቀጥታ ያለፉ የእንግሊዝ ክለቦች ናቸው።

ባየርን ሙኒክ ፣ ባርሰሎና እና የፖርቹጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሌሎች በቀጥታ ያለፉ ክለቦች ናቸው።

በውድድሩ ከ9-24 ያጠናቀቁ ክለቦች የእርስ በእርስ ጨዋታ አከናውነው አሸናፊ ስምንት ክለቦች በቀጥታ ካለፉ ስምንት ክለቦች ጋር የሚፋለሙ ይሆናል።

የባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ፓሪሰን ዠርማ ፣ ሪያል ማድሪድ ፣ ኢንተር ሚላን ጁቬንቱስ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለቀጣይ ጨዋታ ከሚዘጋጁ ክለቦች መሀከል ይጠቀሳሉ። ዕጣ ድልድሉ የፊታችን አርብ ይከናወናል።

ከ25-36 ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ ክለቦች ደግሞ ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ናፖሊ ፣ ማርሴይ ፣ አትሌቲክ ቢልባኦ ፣ አያክስ እና ቪያሪያል ከውድድሩ ውጪ ከሆኑ ክለቦች መሀከል ይጠቀሳሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review