AMN ጥር 21/2018 ዓ.ም
የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ (Agenda 2063) ሰባቱ ዋና ዋና ግቦች
የበለጸገች አፍሪካ፡- በአካታች እድገት፣ ድህነትን በማጥፋት እና በዘላቂ ልማት ላይ የተመሰረተች አፍሪካ፡፡
የተቀናጀች አህጉር፡- በፖለቲካ የተዋሃደች፣ በፓን-አፍሪካኒዝም (Pan-Africanism) እሳቤዎች እና በአፍሪካ ህዳሴ ራዕይ ላይ የተመሰረተች አፍሪካ፡፡
መልካም አስተዳደር፡- ዲሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብቶች፣ ፍትህ እና የህግ የበላይነት የሰፈኑባት አፍሪካ።

ሰላማዊ እና ደህንነቷ የተጠበቀ አፍሪካ፡- ሁሉንም ግጭቶች የማስወገድ ዓላማ ያላት አፍሪካ፡፡
ባህላዊ ማንነት፡- ጠንካራ ባህላዊ ማንነት፣ የጋራ ቅርስ፣ የጋራ እሴቶች እና ስነ-ምግባር ያላት አፍሪካ።
በህዝብ የሚመራ ልማት፡- በአፍሪካ ህዝብ በተለይም በሴቶች እና በወጣቶች አቅም ላይ የሚተማመን ልማት።
ጠንካራ አለምአቀፋዊ ተዋናይ፡- አፍሪካ በአለም መድረክ ላይ የተባበረች፣ የጸናች እና ተጽእኖ ፈጣሪ አጋር ሆና መቅረብ።