AMN- ጥር 21/2018 ዓ.ም
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በቴሌ ብር ከ1.9 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝዉዉሮች መፈፀማቸዉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ያለፉት 6 ወራት አፈፃፀሙን አስመልክቶ መግለጫ እየሰጠ ነዉ፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሰራ አስፈፃሚ ፍሬህይዎት ታምሩ እንደገለጹት ቴሌ ብር እዉን ከሆነ ጀምሮ ከ6.8 ትሪሊዮን በላይ ገንዘብ መዘዋወሩን ገልጸው፣ ባለፉት 6 ወራት ብቻ ከ1.9 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝዉዉር በቴሌ ብር አማካኝነት ተፈፅሟል ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከ87 ሚሊየን የተሻገሩ ስለመሆናቸውም ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ ያለዉ ተደራሽነት የሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ዘመናዊነት እና ቅንጅታዊ ስራ ለደንበኞች ቁጥር ማደግ ትልቁን ድረሻ ይወስዳል ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር