አንጋፋ በጎ ፈቃደኞች ተሞክሮቸውን ለወጣቶች አጋሩ

You are currently viewing አንጋፋ በጎ ፈቃደኞች ተሞክሮቸውን ለወጣቶች አጋሩ

AMN – ጥር 21/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ሁሉም በጎ ፈቃደኞች ለዓላማቸው ጸንተው ሊቆሙ እንደሚገባ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን “የሕይወት ልምዴን ለአዲሱ ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ፣ የአንጋፋ በጎ ፈቃደኞችን ተሞክሮ ለወጣቶች የሚያካፍሉበት መድረክ አዘጋጅቷል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች በጎ ማድረግን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ያደረጉ ግለሰቦች ያላቸውን የዳበረ ልምድ ለሌሎች በጎ ፈቃደኞች ማጋራት መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ይመር ከበደ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም ባለፉት ሰባት ዓመታት በከተማዋ በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ብቻ ከ45 ሺህ በላይ ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች መተላለፋቸውን አስታውሰዋል።

ይህንን የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞች በጀመሩት ቅን ተግባር ላይ በጽናት መቆየት እንዳለባቸውም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከከተማዋ ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች አንጋፋ በጎ አድራጊዎች በሥራቸው ያጋጠሟቸውን ተሞክሮዎችና የሕይወት ልምዳቸውን አጋርተዋል።

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review