“ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚያስፈርመኝ ሳውቅ አልቅሻለሁ” ቡርኖ ፈርናንዴዝ

You are currently viewing “ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚያስፈርመኝ ሳውቅ አልቅሻለሁ” ቡርኖ ፈርናንዴዝ

AMN ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም

ቡርኖ ፈርናንዴዝ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት ነበር በይፋ ማንችስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው። ተጫዋቹ ከሰር አሌክስ ፈርጉሰን መልቀቅ በኋላ ከፈረሙ ተጫዋቾች ምርጡ ተደርጎ ይቆጠራል።

የቡድኑ አምበል ስፖርቲንግ ሊዝበንን ለቆ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የመጣበትን አጋጣሚ ለፕሌይርስ ትሪቡን (The Players’ Tribune) ከወራት በፊት እንዲህ ተርኮት ነበር።

“ወደ ማንችስተር ዩናይትድ እንደምመጣ ያረጋገጥኩበትን አጋጣሚ መቼም ቢሆን አልረሳውም። ሊዝበን በሚገኘው መኖሪያ ቤታችን የመኝታ ክፍል ውስጥ ነበርኩ ፤ ወኪሌ ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ ደወለልኝ ፤ ልጄ ገና ሦስት ዓመቷ ስለነበር የመኝታ ሰዓቷ ደርሶ ተኝታለች ፤ ልጄን ላለመረበሽ ወጣ ብዬ መፀዳጃ አካባቢ ስልኩን አነሳሁት።

ለወኪሌ ከዝውውር ጋር በተያያዘ 100 በመቶ እርግጠኛ ካልሆነ እንዳይደውልልኝ ነግሬዋለሁ ፤ እርግጠኛ ባልሆነበት ዝውውር እራሴን መረበሽ አልፈልግም። ይህን ስለሚያውቅ በዚህ ምሽት የደወለው አንደ የተጨበጠ ነገር ይዞ ነው ብዬ አሰብኩ።

ስልኩን ሳነሳ “ዜናውን ለመስማት ዝግጁ ነህ አለኝ?

ስለምን አልኩት?

ስለ መሄድ የት ማንችስተር ዩናይትድ እየቀለድክብኝ ነው? አልኩት

“አረ በፍፁም ፤ እውነቴን ነው ሁሉ ነገር አልቋል ። የአንተ ምላሽ ብቻ ነው የሚጠበቀው። ምን ታስባለህ? አለኝ።

ምላሽ መስጠት አቃተኝ ፤ ወደ ጉንጬ ካልፈሰስኩ እያለ ካስቸገረኝ እምባዬ ጋር ትግል ጀመርኩ ፤ ስሜቴን ደብቄ ለማውራት ብሞክርም አልቻልኩም።

ወኪሌ ስልኩ ላይ “ቡርኖ ፣ ቡርኖ ቡርኖ ” ይላል በዚህ ጊዜ ባለቤቴ መጥታ ተመለከተችኝ ፤ “ምንድነው ለምን እዚህ መፀዳጃ ቤት አካባቢ ሆንክ? አለችኝ።

ወኪሌ ሚጉኤልን እያወራሁት ነው። ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ ። ” አልኳት

“እንዴ ቆይ እያለቀስክ ነው ታዲያ?” ጠየቀችኝ

“እኔንጃ ምናልባት ደስታ ይሆናል።” አልኳት።

ማንችስተር ዩናይትድ እንደሚፈልገው ሲያውቅ በዚህ መልኩ ስሜቱን የገለፀው ቡርኖ ፈርናንዴዝ በውጣ ውረድ የተሞሉ ስድስት ዓመታትን አሳልፏል።

የሚወደውን ክለብ በአምበልነት የሚመራው የ31 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ 312 ጨዋታ አከናውኖ 103 ግቦችን ሲያስቆጥር 97 ግብ የሆኑ ኳሶችን ደግሞ አቀብሏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review