ሁለተኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ሰፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀምራል

You are currently viewing ሁለተኛው ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ሰፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀምራል

AMN ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት የተማሪዎች ስፖርት ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር ከጥር 23 እስከ የካቲት 08 እንደሚከናወን ተገልጿል።

ውድድሩን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የውድድሩ አላማ ተማሪዎችና መምህራን በተደራጀ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎአቸውን ማሳደግና የተማሪዎችና የመምህራን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር ሀገራዊ ስሜትና ብሔራዊ መግባባትን ማበልፀግ እንደሆነ በመግለጫው ተነስቷል።

በተጨማሪ በሚካሄደው የስፖርት ውድድር ላይ ተማሪዎችና መምህራን ያላቸዉን ችሎታ እንዲያሳዩ ማድረግና ምርጥ ተማሪዎችና መምህራንን ማፍራት አላማው እንደሆነ ተጠቅሷል።

“በአካል ብቁና በአእምሮ ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ውድድር ላይ በእግር ኳስ ፣ ቮሊቦል ፣ አትሌቲክስ ፣ ፓራሊምፒክ ፣ ቼዝ ፣ ዳማና ጠረጴዛ ቴኒስን ጨምሮ በተማሪዎች ደረጃ በስምንት የስፖርትና በመምህራን ደረጃ ደግሞ በሰባት ዘመናዊ የስፖርት አይነቶችና በባህል ስፖርት ገበጣ ፣ ሻህና ቡብ ዉድድሮች በሁለቱም ፆታ ይደረጋሉ::

ከሁሉም ክፍለ ከተሞችና ከሶስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የአንደኛና የመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚጀመር ይሆኗል።

በአዲሱ መንገሻ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review