የገበታ ለትውልድ ዋነኛ ፕሮጀክት የሆነው የሸበሌ ሪዞርት ተመረቀ

You are currently viewing የገበታ ለትውልድ ዋነኛ ፕሮጀክት የሆነው የሸበሌ ሪዞርት ተመረቀ

AMN- ጥር 23/2018ዓ.ም

የሸበሌ ሪዞርት የገበታ ለትውልድ ዋነኛ ፕሮጀክት ሲሆን በ385 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው፡፡

በአንድ ጊዜ እስከ 400 እንግዶችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት ምግብ ቤቶች፣ ልዩ የባሕል ማዕከል፣ ዘመናዊ የክብረ-በዓላትና የስብሰባ አዳራሾች፣ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችና 15.4 ኪሎ ሜትር የሚረዝሙ የእግረኛ መንገዶችን የያዘው የሸበሌ ሪዞርት፤ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከር ታሳቢ ተደርጎ የተገነባ ነው።

10,000 የፍራፍሬ ተክሎች ካረፉበት የፍራፍሬ ፓርክ ጀምሮ እስከ ዋናው የግመል ፓርክ ድረስ፤ እያንዳንዱ የሪዞርቱ ገጽታ የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሐብት የሚያንፀባርቅ ነው።

default

በ51 የተጠናቀቁ የመኝታ ክፍሎችና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ የቱሪዝም አገልግሎቶች እውን የሆነው ሸበሌ ሪዞርት፤ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ታሪካዊ እጥፋት ነው።

ይህ ፕሮጀክት ህልምን ወደ እውነት የመለወጥ፤ የኢትዮጵያን የተፈጥሮና የባህል ጸጋዎች መላው ዓለም የሚካፈለው ቅርስ የማድረግ የመደመር መንፈስ በተግባር የታየበት ታላቅ ስራ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በይፋ መመረቁን ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review