AMN ጥር 23/2018 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በ86ኛው ዓመት የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል አከባበርና በአስደናቂው የፈረስ ትዕይንት ላይ እንደሚታደሙ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የጀግኖች ምድር፣ የደግነት፣ የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ፤ በልምላሜዋና በሁሉን አምራችነቷ የምትታወቀው የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ዋና ከተማ እንጅባራ ገብተናል ብለዋል፡፡
“አዲናስ” ብሎ በፈገግታ የተቀበለንን፣ እንግዳን እንደ ፈጣሪ ስጦታ አክብሮ የማስተናገድ ጥንታዊ ባህሉንና ፍቅሩን በተግባር ላሳየን የአገው ምድር ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ላሳያችሁን ፍቅርና ክብር ያለን አክብሮት ላቅ ያለ ነው።
በቆይታችን የኢትዮጵያ አንዱ ጌጥና ኩራት የሆነውን፣ የአዊን የጀግንነት ታሪክ፣ ባህልና ወኔ የሚመሰክረውን የ86ኛው ዓመት የአገው ፈረሰኞች ማህበር በዓል አከባበርና አስደናቂውን የፈረስ ትዕይንት የምንታደም ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡