የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ የሆላንድ ዜጎችን እና ሁለት ኢትዮጵያንን አግተው ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

You are currently viewing የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ የሆላንድ ዜጎችን እና ሁለት ኢትዮጵያንን አግተው ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

AMN ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ እና ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ ሁለት የሆላንድ ዜጎችን እና ሁለት ኢትዮጵያንን አግተው ሲዘርፉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥርና የአደጋ ምርመራ መምሪያ ባልደረባ ምክትል ኢንስፔክተር በሪሁን ፈንቴ እንጦጦ ፓርክ አካባቢ በስራ ስምሪት ላይ እያሉ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም በመልበስ እና ሀሰተኛ መታወቂያ በመያዝ የሆላንድ ዜግነት ያላቸው ሁለት ሴቶችንና ሁለት ኢትዮጵያውያንን አግተው የዝርፊያ ወንጀል በመፈጸም ላይ እንዳሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውለው ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስረክበዋል።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለማምለጥ ሲሞክሩ ገደል ውስጥ ገብተው የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review