AMN- ጥር 24/2018 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር መንዳይ ሰማያ ኩምባ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው፣ በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እየተደረጉ ያሉ ተከታታይነት ያላቸው ጉብኝቶች፣ የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን ጥልቅ እና ጠንካራ ግንኙነት አመላካች መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይም የበለጠ የሁለቱን አገራት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የበለጠ ማላቅ እንዲሁም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው ሰላም እና ደኀንነት የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ ሀሳብ በመለዋወጥ በቀጣናው ውስጥ መረጋጋትን እና ትብብርን ለማራመድ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።