AMN ጥር 25/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ም/ቤቱን በነገ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፌዴራል መንግስት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ የሚያዳምጥ ይሆናል።

የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በAMN እና AMN PLUS ቴሌቪዥን: በFM 96.3 : በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን በፌስ ቡክና በዩቲዩብ በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።