በ 2050 አብዛኛው አፍሪካዊ ፣ አብዛኛው የዓለም ህዝብ ከተሜ ይሆናል፤ ከተሜነት ይስፋፋል። ይህ አይቀሬ ጉዳይ ነው። በኢትዮጵያ በከተሜነት ግንባታ በኮሪደር ልማት እየመጣ ያለው ለውጥ የማይታየው አንድ ዜጋ ካለ ያሳዝናል።
አዲስ አበባ ብቻ አይደለም በመላ ሀገሪቱ እንቅስቃሴው አለ። ከቢሮ ፣ ከግቢ በመጀመር አዲስ አበባ ላይ ከዛም ወደ ሁሉም አካባቢዎች እናሰፋለን ባልነው መሰረት ፣ በገባነው ቃል መሰረት ከቢሮ የጀመርነው ስራ አሁን ላይ ብዙ ከተሞችን አዳርሷል።
በየከተማው በዕቅድ የሚመራ የሚኖርበት እና የሚሰራበት አካባቢ ካልፈጠርን ሁሉም ወደ አንድ ከተማ ካልመጣ ሲጀመርም በቂ ፕላን እና መሰረተ ልማት ስላልነበረ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ችግሩን ያባብሰዋል።
ትልቅ ህዝብ ያለው ሀገር ስለሆነ በርከት ያሉ ከተሞችን በመፍጠር ፣ ከተሜነት እየተፈጠረ ሲሄድ በከተማ ውስጥ ጤናማ ህይወት መኖር የሚችሉ ፣ አካባቢያቸውን የሚወዱ፣ በሰላም ወጥተው የሚገቡ ፣ በቂ አገልግሎት የሚያገኙ ዜጐች ይበራከታሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጡት ማብራሪያ