AMN – ጥር 26/2018 ዓ.ም
በነዋሪዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን በአግባቡ በመመለስ ህዝብ ተኮር ፕሮጀክቶች በስፋት ይሰራሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት ለ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ዋና ጉባኤው በ29/05/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ጠቅሰው፤ ቅድመ ጉባኤው በዋና ጉባኤው የሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ላይ በቂ ዝግጀት ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ስራዎችን መሰረት በማድረግ የፊት ለፊት ውይይት ላይ የተነሱ ጥያቄዎች እና ጠንካራና ደካማ ጎኖች ላይ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር የተነሱ ጥያቄዎች ምን ያህል ታች ድረስ ወርደው ተሰርተዋል፣ የሚቀሩ ተግባራትስ ምንድን ናቸው፣ በምን ያህል ጊዜስ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው የሚሉ ሀሳቦች ላይ የጋራ መግባባቶች የሚያዙበት ቅድመ ጉባኤ መድረክ መሆኑን ወ/ሮ ቡዜና ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ በየዘርፉ የተሰሩ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ቡዜና፣ ተወያይቶ እነዚህን ፕሮጀክቶች ለማስቀጠል እንዲሁም የታዮ ክፍተቶች ካሉ ለማረም ቅድመ ጉባኤው ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በንጉሱ በቃሉ