የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣዩ አምስት ዓመታት በአመራርነት የሚያገለግሉ መሪዎችን መረጠ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በቀጣዩ አምስት ዓመታት በአመራርነት የሚያገለግሉ መሪዎችን መረጠ

AMN ጥር 28 /2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጥር 28 2018 ዓ.ም ባደረገዉ 5ኛ መደበኛ ጉባኤ በካውንስሉ ውስጥ በቀጣዩ አምስት ዓመታት በአመራርነት የሚያገለግሉ መሪዎች ምርጫ አካሂዷል።

በተደረገው ምርጫም ላለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉትን ጣሰው ገብሬን (ዶ/ር) በመተካት ቄስ ደረጄ ጀንበሩ ለቀጣዩ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ላለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉትን ሐዋሪያ ዮሐንስ ግርማን በመተካት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ እና በድጋሚ ዶክተር ቤተ መንግስቱ ለቀጣዩ ዓምስት አመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዚደንት በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

ላለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሓፊ የነበሩትን ቄስ ደረጄ ጀንበሩን በመወከል ፓስተር ጌትነት ለማ (ዶ/ር) ለቀጣይ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ በመሆን እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ለተመረጡት መሪዎች መልካም የስራ ዘመንን መመኘቱን ከካዉንስሉ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review