AMN ጥር 28/2018
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ክልላዊና ሀገራዊ የምክክር አጀንዳዎቹን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስረክቧል።
የድርጅቱን አጀንዳዎችም የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራሮች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራር አባላት ጋር በአዲስ አበባ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አርዓያ፣ የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች እና የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) አመራር አባላት ተሳትፈዋል።