AMN ጥር 28/2018 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በትጋት የሚሰሩ ክንዶች ሌማታቸውን አትረፍርፈዋል ! ወደፊትም ያትረፈርፋሉ ሲሉ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የሌማት ትሩፋት መንግስት ለዜጋ እና ለሀገር ያለውን ክብር ያሳየበት ልዩ እሳቤ እና ትግበራ ነው ብለዋል፡፡
መንግስት በሌማት ትሩፋት ዘላቂ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፖሊሲ ትግበራ ተደማሪ አቅም በማድረግ ሰርቷል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምዕናብ ልህቀት ፈልቆ የተጀመረው ኢኒሼቲቭ የብዙ ቤተሰብን ሕይወት ቀይሯል፣ ደግሞም ወደፊትም መቀየሩን ይቀጥላል፡፡
የሌማት ትሩፋት ለዘመናት ጸጋ ሆነው ያልታዩ ጓሮዎችን የልማት ከባቢ አድርጓል፡፡ በመሆኑም የተመጣጠነ ምግብ በሽታ መከላከልን ካስቀደመው የጤና ፖሊሲያችን ጋር ግንኙነቱ ቀጥተኛ ነው፡፡ በዚህም የመደመር እሳቤ ባፈለቀው የፈጠራ ተግባር የእንስሳት ተዋጽኦ በአግባቡ ወደ ሌማታችን አምጥቷል ብለዋል፡፡
የሌማት ትሩፋት የተሳሰረው ከከበረ የሰዎች ከሕይወት እና ጤና እንዲሁም ከትልቁ የሃገር መልክ እና ክብር ብሎም ከዘላቂ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ርዕያችን ጋር ነው፡፡
በትጋት የሚሰሩ ክንዶች ሌማታቸውን አትረፍርፈዋል ! ወደፊትም ያትረፈርፋሉ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡