AMN- ጥር 28/2018 ዓ.ም
በመላ ሀገሪቱ አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የኢትጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 52.26 ቢሊየን ብር መሰብሰቡንም ገልጿል።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 54.2 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቀዶ 52.26 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው ገልጸዋል፡፡
በግማሽ ዓመቱ 63 አዳዲስ የገጠር ቀበሌዎች እና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም የገጠሩን ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ይህንን አፈጻጸም ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚያገኙ ደንበኞች ቁጥር እያደገ መምጣቱን በመግለጫው ተመላክቷል፡
በአልማዝ ሙሉጌታ