ባለፉት 5 ዓመታት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያሳደጉ ስራዎች እውን ማድረግ ተችሏል

You are currently viewing ባለፉት 5 ዓመታት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያሳደጉ ስራዎች እውን ማድረግ ተችሏል

AMN- ጥር 28/2018 ዓ.ም

ባለፉት 5 ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት የወጣቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ያሳደጉ ስራዎች እውን ማድረግ ተችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን ተናገሩ ::

ቢሮው ከሲቪክ ማህበራት አደረጃጀቶች ጋር ባለፉት አምስት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡:

የቢሮው ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የወጣቱን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተሰርተዋም ብለዋል።

በዚህም ተግባርም 1.6 ሚሊየን ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሯልም ሲሉ አክለዋል፡፡:

ሌላው ወጣቶች ባለፉት ዓመታት ፖለቲካዊ ተሳትፎቸው እንዲጎለብት በተሰራው ስራም በተለያዩ ተቋማት በአመራርነት እና በውሳኔ ሰጭነት ላይ እንዲሰማሩ መደርጉንም ኃላፊው አብራርተዋል::

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እና ፍትሃዊ እንዲሆን የሲቪክ ማህበራትና ወጣቶች ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አቶ በላይ አሳስበዋል::

ባለፉት 5 ዓመታት ብቻም በድግግሞሽ 4.3 ሚሊየን ወጣቶች በተለያዩ በጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ መሳተፋቸውም በመድረኩ ተመላክቷል::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review