AMN- ጥር 28/2018 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት 39ኛው የመሪዎችን ጉባኤ በብቃት ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማጠናቀቋን ገልጸዋል።
በመጭው የካቲት 4 እና 5 2018 ዓ.ም 48ኛው የአፍሪካ አስፈጻሚዎች ወይም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ጉባዔ የሚካሄድ ሲሆን የካቲት 7 እና 8 2018 ዓ.ም ደግሞ 39ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ይካሄዳል።
የካቲት 6 ደግሞ የጣሊያን አፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንደሚካሔድም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ሁሉንም ጉባዔዎች በብቃት ለመከወን አስተማማኝ የይዘት እና የሎጅስቲክ ዝግጅት አጠናቃለችም ብለዋል።
ሀገራችን ገጽታወን ለማስተዋወቅ፣ በኢኮኖሚ፣ ዲፕሎማሲ እና በፖለቲካ ዲፕሎማሲ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ጉባዔውን እንደምትጠቀምበትም አምባሳደር ነብያት ገልጸዋል።
የአዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌትነት ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ነብያት ሁሉም ዜጋ ለሀገሩ አምባሳደር በመሆን ለጉባዔው መሳካት የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያበረክትም ጥሪ አቅርበዋል።
በይታያል አጥናፉ