ባለፉት 6 ወራት በቤት ልማት ሥራ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት በቤት ልማት ሥራ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥር 29/2018 ዓ.ም

ከቤት ልማት አቅርቦት አንጻር በመንግስት በጀት እና በበጎ አድራጎት ከ12 ሺህ 257 በላይ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን ለልማት ተነሺዎች፣ ለሀገር ባለውለታዎች፣ በጨረታና በመልካም አስተዳደር ማስተላለፍ መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከለውጡ ወዲህ ከ45 ሺህ 5 መቶ በላይ ቤቶች የተገነቡ ሲሆን ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት 4 ሺህ 990 ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።

በመንግስትና የግል አጋርነት እና በከተማው በጀት ሊገነቡ ከታቀዱ 100 ሺ ቤቶች ላይ 97 ሺህ ቤቶች ባለፉት 6 ወራት ወደ ግንባታ ሒደት የገቡ ሲሆን፣ሁሉንም በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየየተደረገ ነው ብለዋል።

በግል እና ሪል ስቴት የሚገነቡ ቤቶች ክንውን 13 ሺህ 517 የደረሰ ሲሆን፣ በኮሪደር የለሙ 810 የንግድ ቤቶችንም በልማት ለተነሱ አነስተኛ ነጋዴዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ከለውጡ በፊት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች መገንቢያ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው የቦንድ ብድር ከወለዱ ብር 61ነጥብ 2 ቢሊየን ከለውጡ ወዲህ መክፈል ተችሏልም ብለዋል።

የመንግስት እና የግል አጋርነት ለማሳደግ በተሰራው ዘርፈ ብዙ ስራ ከ70 በላይ የመንግስትና የግል አጋርነት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፣ ከብር 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን በላይ ካፒታል ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉን አብራርተዋል።

በሚካኤል ኅሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review