AMN ጥር 29/2028 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት ድንገተኛ የእሳትና አደጋ ስጋትን ከመከላከል እና ከመቆጣጠር አንጻር ለ325 አደጋዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለምክር ቤት አባላት እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ በዘላቂነት የአደጋ ስጋት ምላሽን ማጠናከር የሚያስችል ፈንድ መሰብሰብና ማስተዳደር የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት የአሠራር ስርዓት ዘርግቷል።

30 ሚሊዮን ብር በገንዘብ፣24 ሚሊዮን በአይነት፣464 ኩንታል ስትራቴጂክ ክምችት፣ 413 ኩንታል ምግብ ነክ ክምችት በመያዝ ከ110 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የመጠባበቂያ ክምችትና ገንዘብ መሰብሰቡን ተናግረዋል።
በዚህም የአደጋ ምላሽ በራስ አቅም ለማቅረብ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ ማከናወን ተችሏል ብለዋል።
በትዝታ መንግስቱ