ለልማት ተነሺዎች ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ካሣ መከፈሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing ለልማት ተነሺዎች ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ካሣ መከፈሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN – ጥር 29/2018 ዓ.ም.

ባለፉት ስድስት ወራት ለልማት ተነሺዎች ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ካሣ መከፈሉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። ለልማት ተነሺዎቹ።

የቅድመ ማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 54 ባለይዞታዎች በይዞታቸው ላይ ማልማት እንዲችሉ ውሳኔ መሰጠቱንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡ ከመሬት ልማት እና አስተዳደር ጋር በተያያዘ የኦንላይን አገልግሎትን ለማሳለጥ ባለፉት ስድስት ወራት 13,669 ካርታዎች ታትመው መሰራጨታቸውን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ውስጥም በተሻሻለው ሲስተም 10,528 ካርታዎች ታትመው ተሰራጭተዋል፡፡

የለማ መሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ሥርዓትን ከማሻሻል አንጻር ለተለያዩ አገልግሎቶች 341 ሔክታር መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ ከ465 ሔክታር በላይ መሬት ማዘጋጀት መቻሉንም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።ይህም በአፈጻጸም ከ100 በመቶ በላይ እንደሆነ ነው የተነሳው፡፡

በተያያዘ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውልና የከተማዋን ፍላጎት ያማከለ 294.20 ሔክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ ከ483 በላይ ማስተላለፍ መቻሉም ጠቅሰዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ አዲስ እና ነባር ግንባታዎችን ቁጥጥር እና ክትትል በተመለከተ ለ5,616 አዲስ የግል እና የመንግስት ግንባታዎች ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ 5,394 ግንባታዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ተችሏል፡፡ በ3,252 ነባር የግል እና የመንግስት ግንባታዎች ላይ ደረጃ የማስተካከያ አርምጃዎች መወሰዳቸውም ተነስቷል፡፡

ይህም ግንባታዎች በከተማዋ የሚከናወኑት በዘፈቀደና በአልሚው ፍላጎት ብቻ ሳይሆን በጸደቀው የከተማዋ ስታንዳርድ እና የአካባቢ ልማት ጥናት ላይ በመመስረት መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review