ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገ ነዉ

You are currently viewing ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገ ነዉ

AMN ጥር 30/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ንግድ ቁጥጥር እና ፍትሀዊነት በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ያለአግባብ ዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ምክንያት የሚፈጠር የአቅርቦት እጥረትን ለመከላከል አስተዳደሩ የንግድ ኮርፖሬሽን አቋቁሟል።

በዚህም ነጋዴዎች ያለአግባብ ዋጋ ሲጨምሩ ከሚደረጉ የቁጥጥር ስራዎች በተጨማሪ የንግድ ኮርፖሬሽኑ ምርት በማቅረብ የአቅርቦት ፍላጎትን ማረጋጋት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሕገ ወጥ የንግድ አሰራሮችን ለመቆጣጠር ከሚወሰዱ እርምጃዎች ጋር ተያይዞ ለሚነሱ የአሰራር ብልሽቶች ጉዳዩን በትኩረት ይዘን እንዲፈታ እና አሰራሩ ላይ ማሻሻያ እንዲኖር እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ከዘይት አቅርቦት ጋር በተያያዘ አስተዳደሩ 8.8 ሄክታር ላይ የሚያርፍ ፋብሪካ ግንባታ ከ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር ማመቻቸቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪ በለሚ ኩራ ሰፊ እና ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review